ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለልማት እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የጎላ ድርሻ እንዳለው ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለፁ

You are currently viewing ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለልማት እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የጎላ ድርሻ እንዳለው ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለፁ

AMN- ሐምሌ 19/2017 ዓ.ም

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በተጀመረው 4ኛው ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ለሆኑ ወጣቶች የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስጋናና ዕውቅና መርሐ-ግብር አካሂዷል።

በእውቅና አሰጣጥ መርሀ-ግበሩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ ወጣቱ እያከናወነ የሚገኘው ወሰን ተሻጋሪ ሀገር አቀፍ የበጎ ፍቃድ ተግባር የሀገር ልማትን ለማፋጠንና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ድርሻው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙና አህመድ፣ ወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የሰላም፣ የአብሮነት ማጠናከሪያ ፣ የብዝሃነት መገለጫ እና የወጣቶች ለሀገር የመቆም ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ወጣቶቹ በተለያዩ ክልሎችና የሀገራችን አካባቢዎች ተዘዋውረው አገልግሎቱን በሚሰጡበት ወቅት የማህበረሰቡን መልካም እሴት እንዲያውቁ ዕድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል፡፡

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ባህል እየሆነ የመጣው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከመፍታት ባለፈ ለህዝቦች ማህበራዊ ትስስር መጎልበት ምቹ አጋጣሚ ፈጥሯልም ነው ያሉት።

የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ የተሳተፉ ወጣቶችም በዚህ የመልካም ስራ ተግባር ላይ ተሳታፊ መሆናቸው የተለያዩ የኢትዮጵያን ባህል፣ ወግና እሴቶችን ለማወቅና የሀገር ፍቅር ስሜታቸውን ለማጠንከር እንደረዳቸው ተናግረዋል፡፡

በደሳለኝ ሙሐመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review