የመሬት ወረራን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የሚያስችል ስራ መሰራቱን የንፋስ ስልክ ለፍቶ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
ክፍለ ከተማው በ2017 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘቡ የወረዳ ጽሕፈት ቤቶች፣ ሰራተኞች እና ባለድርሻዎች እውቅና ሰጥቷል።
በመርሐ-ግብሩ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ አለሙ፣ በበጀት ዓመቱ በክፍለ ከተማው የደንብ መተላለፍን ለማስቀረት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።
እውቅናው በብዙ ጥረትና ትጋት የመጣ እንደሆነም ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻአለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ለደንብ መተላለፍ ምክንያት የሆኑ ተግዳሮቶችን ለማስቀረት ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል።
ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገቡ ከከተማ አስተዳደሩ እውቅና አግኝቷልም ብለዋል።
ተግባሩ በ2018 በጀት ዓመትም በትጋት የሚሰራበት መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል።
በፂዮን ማሞ