የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋናው መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋናው መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

AMN- ሐምሌ 19/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋናው መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በዋናው መስሪያ ቤት እና በቦሌ በለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በዛሬው ዕለት የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር አካሂደዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በመላ ሀገሪቱ የሚገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲስትሪክት ጽሕፈት ቤቶች እና ቅርንጫፎች እንዲሁም የዋናው መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ችግኞችን እንደሚተክሉ ባንኩ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ፣ ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባለፉት ዓመታት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በመትከልና በመንከባከብ እየሰራ መቆየቱን ጠቅሰዋል።

በችግኝ ተከላ መርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን በመንከባከብም ግዴታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review