ዓለም አቀፍ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ኮንፍረንስ በሻንጋይ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing ዓለም አቀፍ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ኮንፍረንስ በሻንጋይ እየተካሄደ ነው

AMN- ሐምሌ 19/2017 ዓ.ም

“ዓለም አቀፍ ወንድማማችንት፣ በኤ አይ ዘመን” በሚል መሪ ሀሳብ ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ኮንፍረንስ እና የኤ አይ አስተዳደር ላይ ያተኮረ መድረክ በምስራቃዊ ቻይና በምትገኘው ሻንጋይ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በተሳታፊ እና በተጋባዥ እንንግዶች ብዛት፣ በኤግዚቢሽን ስፋት እና በአዳዲስ ምርቶች ትውውቅ ረገድ እስከ አሁን ከተካሄዱት ኮንፍረንሶች እንደሚለይ ተገልጿል፡፡

ለኤግዝቢሺኑ የተዘጋጀው ቦታ 70 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፣ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤት የሆኑ ሮቦቶችን ጨምሮ 3ሺ ምርጥ የተባለላቸውን ምርቶችን የሚያቀርቡ 800 ድርጅቶች በኮንፍረንሱ ይሳተፉበታል፡፡

ከ100 የሚልቁ አዳዲስ ምርቶች በኮንፍረንሱ ላይ ለውድድር ይቀርባሉ ተብሏል፡፡

ከ30 በላይ ሀገራት የተጋበዙ ከ1ሺህ 200 በላይ እንግዶች የሚገኙበት ኮንፍረንሱ በ3 ቀናት ቆይታው በርካታ ፎረሞችን የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡

ለ8 ተከታታይ ዓመታት የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፍረንስ ስታስተናግድ የቆየችው የሻንጋይ ከተማ በኤ አይ ልማትና አስተዳደር ረገድ ግንባር ቀደምነቷን አጠናክራ ቀጥላለች፡፡

በተያዘው የፈረንጆቹ 2025 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ የከተማዋ የአርተፊሻ ኢንተለጀንስ ኢንዱስትሪ ምርት መጠን 16.5 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም በየዓመቱ የ29 በመቶ እድገትና 65 በመቶ ትርፍ የምታገኝበት መሆኑን የሲጂቲኤን ዘገባ አመለክቷል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review