የዓለም የእርሻና ምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ በ2ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ሳህረላ አብዱላሂ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ማድረጋቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።
በተመሳሳይ በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ የኬንያ ቀዳማዊት እመቤት ራቸል ሩቶ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፤ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሩያ አሊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ኢትዮጵያ፣ ከጣሊያንና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በጋራ ያዘጋጁት ሁለተኛው የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ከሐምሌ 20 እስከ 22/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
በመጀመሪያው የዓለም የምግብ ሥርዓተ ጉባኤ ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በጉባኤው የሚሳተፉ የሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።