ኢትዮጵያ ለስርዓት ምግብ የሰጠችው ትኩረት የሚደነቅ መሆኑን በ2ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ተሳታፊዎች ገለፁ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ለስርዓት ምግብ የሰጠችው ትኩረት የሚደነቅ መሆኑን በ2ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ተሳታፊዎች ገለፁ

AMN – ሐምሌ 20/2017 ዓ.ም

በ2ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ለመታደም አዲስ አበባ የገቡ ተሳታፊዎች ኢትዮጵያ በምግብ ትራንስፎርሜሽን እያከናወነቻቸው የሚገኙ ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

ተሳታፊዎቹ የጉለሌ የተቀናጀ የልማት ፕሮጀክት አካል የሆነውን ጉለሌ እንጀራ መጋገሪያ ማዕከል ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ኢትዮጵያ ለስርዓት ምግብ የሰጠችው ትኩረት የሚደነቅ ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ ለሴቶች በልዩ ሁኔታ ስራ እድል በመፍጠርና የሴቶችን አቅም ለማጎልበት ጉለሌ እንጀራ መጋገሪያ ማዕከል ላይ የተመለከቱት ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ተሞክሮ ለተቀረው ዓለም ለማካፈል ጉብኝታቸው ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም አስተያየታቸውን ለኤ ኤም ኤን ሰጥተዋል።

በይታያል አጥናፉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review