የህፃናትን የፈጠራ እና የማሰላሰል አቅም የሚጨምሩ በጨዋታ መልክ ለማስተማር የሚያግዙ በርካታ መጫወቻዎች ከሎጎ ፋዉንዴሽን በክሊቲን ሐልዝ አክሰስ ኢንሼቲቭ በኩል ተበርክቶልናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፁ

You are currently viewing የህፃናትን የፈጠራ እና የማሰላሰል አቅም የሚጨምሩ በጨዋታ መልክ ለማስተማር የሚያግዙ በርካታ መጫወቻዎች ከሎጎ ፋዉንዴሽን በክሊቲን ሐልዝ አክሰስ ኢንሼቲቭ በኩል ተበርክቶልናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፁ

AMN – ሐምሌ 20/2017 ዓ.ም

ዛሬ የህፃናትን የፈጠራ እና የማሰላሰል አቅም የሚጨምሩ በጨዋታ መልክ ለማስተማር የሚያግዙ በርካታ መጫወቻዎች ከሎጎ ፋዉንዴሽን በክሊቲን ሐልዝ አክሰስ ኢንሼቲቭ በኩል ተበርክቶልናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።

ከንቲባዋ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት በከተማችን የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ፕሮግራምን ዋነኛ የትዉልድና የአገር ግንባታ ምሶሶ አድርገን በስፋት እየሰራንበት እንገኛለን ብለዋል።

የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ፕሮግራም በክህሎት የዳበረ፣ በፈጠራ የጎለበተ አካባቢዉን በሚገባ የተረዳና ለሚገጥሙት ፈተናዎች አስቀድም ሳይንሳዊ መፍትሔ የሚያበጅ ጠንካራና አገር ወዳድ ትውልድ ለመገንባት ያስችላል ብለዋል።

ፕሮግራሙ ተግባራዊ ማድረግ ከተጀመረ አጭር ጊዜ ቢሆንም በርካታ አገራት ከወዲሁ ውጤቱን በመረዳት ልምድ እየቀሰሙበት እና እየደገፉት እንደሚገኙ አመላክተዋል ።

ስጦታዎቹ የአዕምሮ እድገት ውስንነትና የአካል ጉዳት ያለባቸውን ህፃናት ጭምር ያማከለ በመሆኑ አስተባባሪዎቹን ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review