በ2017 በጀት ዓመት ከ108 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ገለጸ

You are currently viewing በ2017 በጀት ዓመት ከ108 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ገለጸ

AMN ሐምሌ 21/2017

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ በ2017 በጀት ዓመት ከ108 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ(ዶ/ር)፤ በ2017 በጀት ዓመት በተቋሙ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የገቢ መጠን ማሳደግ፣ የመርከቦችንና የጭነት ተሽከርካሪዎችን የመጫን አቅም መጨመር፣ ፈጣንና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት መስጠትና በቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮችን ማጎልበት በበጀት ዓመቱ በትኩረት የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን አንስተዋል።

ከዚህ አንጻር በ2017 በጀት ዓመት 101 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ከ108 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መግኘቱን ገልጸዋል።

ይህም ከእቅዱ አንፃር ሲታይ አፈፃፀሙ ከመቶ ፐርሰንት በላይ ማሳካት መቻሉን ጠቁመዋል።

ይህ ከፍተኛ ውጤት እንዲመዘገብ በቅርቡ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰቱ አለመረጋጋቶች በባህር ትራንስፖርት አገልግሎት እንቅስቃሴ ላይ የፈጠሩትን ጫና በመቋቋም ውጤታማ ስራ መከናወኑን መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review