በምግብ ስርዓት ዙሪያ ያለው ግንዛቤ እያደገ መምጣቱን አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናገሩ

You are currently viewing በምግብ ስርዓት ዙሪያ ያለው ግንዛቤ እያደገ መምጣቱን አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናገሩ

AMN-ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ እያሰናዳች የሚገኘው 2ኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በጉባኤው ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በቪዲዮ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ዋና ፀሃፊው ጉባኤው እውን እንዲሆን የኢትዮጵያ እና የጣልያን መንግስት ላሳዩት ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከመጀመሪያው የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በኋላ የተሻለ ግንዛቤ እንደተፈጠረ የገለፁት ጉቴሬዝ ’’የዓለማችን ሁለት ሦስተኛ ሀገራት በዓለም አቀፍ የእድገት እቅድ ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል ፡፡ ’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review