ሶማሊያ 85 በመቶ የውጭ ንግድ ገቢ የምታገኘው ከግብርናው ዘርፍ መሆኑን የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ ገለጹ

You are currently viewing ሶማሊያ 85 በመቶ የውጭ ንግድ ገቢ የምታገኘው ከግብርናው ዘርፍ መሆኑን የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ ገለጹ

AMN- ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የምግብ ስርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄዱን ቀጥሏል።

በመርሐ-ግብሩም የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ፣ ግብርና ከሴክተርም በላይ ነው ብለዋል።

ይህ ስብሰባ ወቅታዊ ብቻ ሳይሆን በጣም አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ሁሉንም ያካተተ የምግብ ስርዓት ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት ለማሳየት ይጠቅማል ብለዋል።

ግብርና ህልውናችን እና ባህላችን ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ 70 በመቶ GDP እና ለ80 በመቶ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩንም ተናግረዋ።

በተጨማሪም ሀገሪቱ 85 በመቶ የውጭ ንግድ ገቢ የምታገኘው ከግብርና መሆኑን አመላክተዋል።

የሶማሊያ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና የዓሣ አምራች ማህበረሰቦች ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ቢያጋጥምም ሀገሪቱን በመመገብ ረገድ ያሳዩት ጽናት እና ጥንካሬ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

በሶማሊያ የእንስሳት እርባታ የግብርና ኢኮኖሚው ዋና ምሰሶ ብቻ ሳይሆን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ዛሬ ላይ ሶማሊያ አዲስ ብሔራዊ ትራንስፎርሜሽን እቅድ አውጥታ እየተገበረች መሆኑንም ጠቁመዋል።

ግብርና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ሞተር መሆኑን መለየታቸውን በንግግራቸው አስታውቀዋል።

የሀገራዊ የትራንስፎርሜሽኑ ለግሉ ዘርፍ ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑንም አመለካክተዋል።

ትራንስፎርሜሽን እቅዱ በአጠቃላይ ለእሴት ሰንሰለት ማሻሻያ ቅድሚያ የሚሰጥ ፍኖተ ካርታ እንደሆነም አንስተዋል።

የሀገሪቱ መንግስትም የአየር ንብረትን የመቋቋም አቅምን የሚያበረታቱ ፖሊሲዎችን እና መርሐ-ግብሮችን በማውጣት ድህነትን ለማስወገድ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።

በብርሃኑ ወርቅነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review