ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው ያሉ የልማት ስራዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው ያሉ የልማት ስራዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ ገለጹ

AMN- ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው ያሉ የልማት ስራዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሀመድ ገለጹ።

ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ የመክፈቻ መርሐግብር በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ bመካሔድ ላይ ነው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሀመድ፣ በርካታ ሀገራት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተለያዩ እርምጃዎች እየወሰዱ ናቸው ብለዋል።

እንዲሁም መንግስታት በዚህ ላይ ፖሊሲና ስትራቴጂ ቀርጸው እየተገበሩ መሆናቸው በሪፖርት መመላከቱን ጠቁመዋል።

ትናንት ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና ማረጋገጥ እያከናወነቻቸው ያሉ ስራዎች አስደናቂ መሆናቸውን ለመመልከት መቻላቸውን አንስተዋል።

ይህም የአመራሩን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ባለብዙ ወገን ግንኙነትን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ዓለም አቀፋዊ ቀውሶች ሲያጋጥሙም መውጫ መንገድ መሆኑን አብራርተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review