የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም አፍሪካ ዓለም የደረሰበትን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት በራሷ መንገድ በመቀየስ የተስፋ ጎህ እየፈነጠቀባት እንደሆነ ማሳያ መሆኑን የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም አፍሪካ ዓለም የደረሰበትን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት በራሷ መንገድ በመቀየስ የተስፋ ጎህ እየፈነጠቀባት እንደሆነ ማሳያ መሆኑን የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ

AMN- ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም አፍሪካ የኋላቅርነት ትርክትን በመቀየር ዓለም የደረሰበትን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት በራሷ መንገድ በመቀየስ የተስፋ ጎህ እየፈነጠቀባት የምትገኝ አህጉር ስለመሆኗ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካ ጋር በመሆን የሳይንስ ሙዚየምን ጎብኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ጉብኝታቸው በቴክኖሎጂው መስክ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚረዳ አመላክተዋል።

የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም አፍሪካ የኋላቅርነት ትርክትን በመቀየር ዓለም የደረሰበትን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት በራሷ መንገድ በመቀየስ የተስፋ ጎህ እየፈነጠቀባት የምትገኝ አህጉር ስለመሆኗ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

አቶ ተመስገን በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ እና ኩባ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ ጉዳዮች ዙሪያ ትብብራቸውን ለማጠናከር እና በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review