አልጋ በሚያከራዩ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የጦር መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ

You are currently viewing አልጋ በሚያከራዩ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የጦር መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ

AMN- ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

አልጋ በሚያከራዩ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የጦር መሳሪያዎች ከመሰል ጥይቶች ጋር መያዙን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ሚዲያ ባደረሱት መረጃ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የከተማውን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግና አጠራጣሪ ጉዳዮች ባጋጠሙበት ወቅት ጭምር ድንገተኛ ፍተሻና አሰሳ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ልዩ ቦታው 32 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ አልጋ ቤቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ፣ አራት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ከ298 ጥይቶች ጋር መያዙን ገልፀዋል፡፡

ፖሊስ ሁል ጊዜም ህብረተሰቡን የፀጥታ ስራው አጋር በማድረግ የከተማውን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ ሽፍት በማጠፍ ጭምር የወንጀል መከላከል ተግባራቱን እያከናወነ መሆኑንና የተገኘው ውጤትም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን አስታውቋል፡፡

በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳታፊ የነበሩት ፍቃዱ ማናየ፣ አዳነች ጎበዜ፣ ዮሀንስ ፍቃዱ እና ዮናስ በቀለ ላይ ተገቢው ምርመራ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን በማሰባሰብ በህግ አግባብ ለማስጠየቅ እንደሚሰራ ፖሊስ ማስታወቁን ኮማንደር ማርቆስ ገልጸዋል፡፡

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ማዘዋወርም ሆነ መጠቀም በህግ የሚያስጠይቅ ድርጊት መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም በአቅራቢያ ለሚገኝ የፀጥታ አካል መረጃ መስጠት እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review