በመርሃ ግብሩ ላይ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ጨምሮ የጸጥታ ሰራዊት አባላት ተሳትፈዋል፡፡
በመትከል ማሰራት በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው 7ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በርካታ ተቋማት በመሳተፍ አሻራቸውን በማኖር ላይ ይገኛሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሃይማኖት አባቶች ፤ ከመከላከያ ሰራዊት ፤ ከፌደራል ፖሊስ ፤ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ደንብ ማስከበርና ከሰላም ሰራዊት ጋር በመሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ትንሹ አቃቂ ተብሎ በሚጠራው ወንዝ አካባቢ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በዚሁ መርሃ ግብርም የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት የጸጥታ መዋቅሩ ከሰላምና ጸጥታ ስራዎች ጎን ለጎን በሀገራዊ ልማቶች በመሳተፉ ሚናውን እየተወጣ ነው፡፡
አዲስ አበባን ውብና ጽዱ በማድረግ ሂደትም ወንዞች አካባቢ አረንጓዴ አሻራን በማሳረፍ ወንዞች ከብክለት የጸዱ መዲናዋን ለነዋሪዎች የተመቸች እንድትሆን በሚሰራው ስራ ውስጥ ሰራዊቱ እውቅና የሚሰጠው ስራ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይም የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ እንክብከላቤና ክትትል ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡
በችግኝ ተከላው የተሳተፉ የጸጥታ አካላት እና የሃይማኖት አባቶችም በሀገራዊ ልማት የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ለትውልድ የሚሻገር አሻራ በማሳረፋቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
ሁሉም በዚሁ ልማት በመሳተፉ የአካበቢ ጥበቃን ማረጋገጥ ተፈጥሮን መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም ነው የጠቆሙት፡፡
በፍቃዱ መለሰ