ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በቀበና ወንዝ ዳርቻ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በቀበና ወንዝ ዳርቻ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

AMN ሃምሌ 22/2017

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ “በመትከል ማንሰራራት “በሚል መሪ ቃል ዛሬ ማለዳ ከኮሙኒኬሽን እና ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በቀበና ወንዝ ዳርቻ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በኢትዮጵያውያን በጎ የሆነን ሀሳብ የምታሰሮፁ ናችሁና እና አሁንም ስራችሁን እንድታጠናክሩ እላለሁ ብለዋል፡፡

ዛፍ መትከል የዛሬ ብቻ ሳይሆን የነገም ተስፋችን እንዲሁም የምግብ ዋስትናችንን ለነገው ትውልድ የምናረጋግጥበት በመሆኑ በዛሬው መረሀ ግብር የተሳተፋችሁ ከመትከል ባሻገር መልካም ሀሳብ የምታሰርፁ ናችሁና ችግኞችን ከመትከል ባሻገር ትውልድን የማነፅ ስራ እንድትሰሩ አደራ እላለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review