በከተማዋ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የሚፈልገውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

You are currently viewing በከተማዋ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የሚፈልገውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

AMN – ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም

በከተማዋ የሚገኙ ከ 3 ሺህ 700 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የሚፈልገውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ።

የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የባለድርሻ አካላት እውቅና እና የ2018 በጀት ዓመት ቅንጅታዊ አሰራር ከባለድርሻ አካላት በጋራ ለመስራት የሚያስችለዉን የስምምነት ሰነድ ተፈራረሟል፡፡

በ 2017 በጀት ዓመት በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉም ተመላክቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮቶች በጋራ በመፍታት ብቁና ተወዳዳሪ ማድረግ ተችሏል ብልዋል።

በከተማዋ የሚገኙ ከ 3 ሺህ 700 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የሚፈልገውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ገልፀዋል።

በ2017 በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን የተናገሩት አቶ ጃንጥራር፤ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በላይ አልቆ መስራት ይገባል ብለዋል።

በተከናወኑ ተግባራትም የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከነበረበት 60 ከመቶ ወደ ከ66 ከመቶ በላይ ማሳደግ እንደተለቻም በመድረኩ ተመላክቷል።

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review