የመዲናዋ ሴቶች በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተያዘዉ ሃገር አቀፍ መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸዉን ገለጹ

You are currently viewing የመዲናዋ ሴቶች በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተያዘዉ ሃገር አቀፍ መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸዉን ገለጹ

AMN – ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም

የመዲናዋ ሴቶች በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተያዘዉ ሃገር አቀፍ መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸዉን ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በየደረጃው የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ሴት አመራሮችን በማስተባበር በአዲስ አበባ ከተማ የአካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ልማት ማዕከል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዷል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉት ሴት አመራሮችም በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተያዘዉ ሃገር አቀፍ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ አሻራቸዉን ለማኖር ዝግጁ መሆናቸዉን ለኤ ኤም ኤን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፤ ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ የመዲናዋ ሴቶች ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር በሚከናወነው የ700 ሚሊዮን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ በነቂስ ወጥተዉ አሻራቸዉን እንዲያኖሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review