በአሜሪካ እና አውሮፓ ሕብረት መካከል የተደረሰው አዲሱ የንግድ ስምምነት፣ አውዳሚ የንግድ ጦርነትን እንደ መከላከል ነው ሲሉ የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚሼል ማርቲን ገለጹ፡፡
ስምምነቱ እጅጉን ተባብሶ ሊቀጥል የሚችለውን መካረር እና የሁለቱንም ኢኮኖሚ ሊያቃውስ የሚችል የንግድ ግጭት መከላከል የቻለ መሆኑን ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
በአሜሪካ እና አውሮፓ ሕብረት መካከል በተለያዩ ወሳኝ ጉዳይ ላይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል በር የከፈተ ነውም ብለዋል፡፡
እኛ ክፍት የንግድ ኢኮኖሚ እንዳለ እናምናለን ያሉት ማርቲን፣ ታሪፍን ከመሠረቱ እንቃወማለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ከእንግዲህ የአውሮፓ ፈተና በአንድ ገበያ ውስጥ ያሉ እንቅፋቶችን መቀነስ፣ በፍላጎት እና በይበልጥ ንቁ የሆነ የንግድ ልውውጥ፣ የንግድ ስምምነቶች ላይ ወደፊት መግፋት እና የገበያ ብዝሃነትን የማመቻቸት ጉዳይ እንደሚሆንም እንስተዋል፡፡
ዋናው ጉዳይ የንግድ ጦርነትን ማስቆም እስከሆነ ድረስ ግን የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን የደረሰበትን ውሳኔ አደንቃለሁ ማለታቸውን አር ቲ ኢ ነው ነው የዘገበው፡፡