ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መገኛ እና የወርቅ ምድር በሆነችዉ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አረንጓዴ አሻራቸዉን ማኖራቸዉን ገልጸዋል።
መትከል ማንሰራራት ጉዟችን ዛሬም በታላቁ ህዳሴ ግድብ መገኛ እና በወርቋ ምድር ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቀጥሏል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ ስራችን ምግብ የምናመርትበት፣ በቅጠሎቹ በረሃማነትን፣ በስሮቹ ደግሞ የአፈር መሸርሸርን የምንከላከልበት ጋሻችን ነው።
ዛሬ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተከልናቸው ችግኞች ከጥላነት የተሻገረ ፍሬ የሚሰጡ፣ ከዛፍነትም ያለፉ የውሃችን ጠባቂ ዘብ ናቸው።
አረንጓዴ ዐሻራ ለተፈጥሮ ሰላም እና ደህንነት የሚሆን ብርቱ ሰልፍ ነው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ መልእክት አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም በአሶሳ ከተማ ዛሬ የጎበኘናቸው የተቀናጀ የኮሪደር ልማት ሥራዎቹ የከተማዋን ገፅታ፣ ዘመናዊነትና የነዋሪዎቿን ኑሮ የሚያሻሽሉ ናቸው፡፡
በአሶሳ ከተማ የሞቀ አቀባበል ላደረጉልን የክልሉ ፕሬዝደንት እና ካቢኒያቸው ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ሲሉ ገልጸዋል።