ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጪው ሀሙስ በጋራ ታሪክ እንስራ ሲሉ መልእክት አስተላለፉ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጪው ሀሙስ በጋራ ታሪክ እንስራ ሲሉ መልእክት አስተላለፉ

AMN ሃምሌ 23/2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመጪው ሀሙስ በጋራ ታሪክ እንስራ ሲሉ መልእክት አስተላለፉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያ አረንጓዴ እና ለፈተና የማይበገር ነገዋን ለመገንባት ለምታደርገው ጥረት እንደገና ትነሳለች። ነገ ከንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራችን አካል የሆነውን በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል አላማን ለማሳካት እንነሳለን። ከፍ ያለ ግብ ነው። ግን ጥንካሬያችንን፣ አንድነታችንን እና ለሕዝባችን ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል።

ይኽ ችግኝ ከመትከል በላይ ነው። ትንሽ ትልቅ፣ የከተማ የገጠር ሳንል ዜጎች ሁሉ አካባቢያችን እንዲያገግም፣ የውሃ ምንጮቻችን እንዲጠበቁ፣ የኑሮ ሁኔታችን እንዲሻሻል እንዲሁም ለመጪው ትውልዶች ዘላቂነት ያለው ነገን ለማረጋገጥ የምንሳተፍበት ተግባር ነው።

ሁላችሁም በዚህ ታላቅ ሥራ እንድትሳተፉ እና እንድታስተባብሩ አሳስባለሁ። በጋራ ጠንካራ ዛፎችን ብቻ ሳይሆን ጠንካራ እና የበለጠ አረንጓዴ የሆነች ኢትዮጵያን እናሳድጋለን ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review