የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ተደራሸ የማድረግ ሚናቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተገለጸ

You are currently viewing የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ተደራሸ የማድረግ ሚናቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተገለጸ

AMN ሐምሌ 23/2017

የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ተደራሸ የማድረግ ሚናቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ በብልጽግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) አስገነዘቡ።

“መጪው ጊዜና የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዝግጅታችን” በሚል መሪ ሃሳብ የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎችን ያሳተፈ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በብልጽግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ለውጡን ተከትሎ በተሰሩ ስራዎች ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በፖለቲካው መስክ ምህዳሩ እንዲሰፋ መደረጉን ጠቅሰው፤ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ስራዎች መከናወናቸውን አስታውቀዋል።

ከዲፕሎማሲ አኳያም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ከፍ ያደረጉ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው፤ በዚህም የኢትዮጵያ ተሰሚነት እያደገ መምጣቱን አመልክተዋል።

በማህበራዊ ዘርፍም በሰው ተኮር ስራዎች እና በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ በጉልህ የሚታዩ ውጤቶች መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡

በኢኮኖሚው መስክም እንዲሁ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምክንያት ተጠቃሽ ውጤቶች መገኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡

የተገኙ ስኬቶችን ለህዝብ በአግባቡ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመው፤ ከዚህ አንጻር የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ተደራሽ የማድረግ ሚና ሊጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ብዥታን ከመፍጠራቸው በፊት አጀንዳዎችን ቀድሞ ተደራሽ በማድረግ መቀልበስ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በተጨባጭ የተሰሩ ስራዎችን በተሰራው ልክ ለማሳየት ከፍ ያሉ የይዘት ስራዎችን በተከታታይ ለህዝብ ማድረስ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

የሀገር እና የህዝብ መዳረሻ ግቦች ላይ ትኩረት ያደረጉ ስትራቴጂያዊ እይታ ያላቸው ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም አመልክተዋል።

በተቋማት ህዝብ ግንኙነቶች መካከል በጋራና በተናበበ መንገድ መስራት ቁልፍ መሆኑን ማንሳታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅቱ የሚጠይቀውን የአቅም፣ የቴክኖሎጂ ዝግጅት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህ ረገድ ጊዜውን የሚመጥን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review