ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጅማ ዞን፣ በሻሻ ከተማ ያስገነቡትን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው ቀን መርቀዋል

You are currently viewing ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጅማ ዞን፣ በሻሻ ከተማ ያስገነቡትን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው ቀን መርቀዋል

AMN- ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም

የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት እየተገበራቸው ካሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ውስጥ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ሲሆን ላለፉት 5 ዓመታት በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በአጠቃላይ 34 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ ከ40 ሺህ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ትምህርት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል ዛሬ 35ኛውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስመረቁን አስታውቋል።

በአቅራቢያ ትምህርት ቤቶች በማይገኙባቸው ቦታዎች የተገነቡት በትምህርት ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት፣ ትውልድን በትምህርት ለማነጽ እና የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑም ተገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review