የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሚገባ ተገለጸ

You are currently viewing የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሚገባ ተገለጸ

AMN- ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ የበላይነት ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴ የ45 ቀናት የስራ እንቅስቃሴውን ገምግሟል።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ፣ በ45 ቀናት ውስጥ በምርት አቅርቦት፣ በህጋዊ የንግድ ስርዓትና ግብይት ማስፈን፣ ያለ ንግድ ፈቃድ ይነግዱ የነበሩ ነጋዴዎች ህጋዊ እንዲሆኑ እና ያልታደሰ የንግድ ፈቃድ ይዘው የሚሰሩም እንዲያድሱ የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡

ቢሮ ኃላፊዋ የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ይሰራል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸው፣ የምሽት ንግድን ለማጠናር ማንኛውንም አይነት ህገወጥ ተግባር የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

በምሽት ንግድ ላይ እያጋጠመ ስላለው የትራንስፓርት አቅርቦትና የታሪፍ ጭማሪ ሁኔታ በቅንጅት መፍታት ተገቢ ስለመሆኑም ዋና ስራ አስኪያጁ አሳስበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበከሉላቸው፣ ባለፉት 45 ቀናት በግብረ ሀይሉ በኩል ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው፣ ውጤት ባልተመዘገበባቸው ዘርፎች ላይ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

በጽዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review