ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በሶማሌ ክልል እናሳርፋለን ሲሉ ገለጹ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በሶማሌ ክልል እናሳርፋለን ሲሉ ገለጹ

AMN ሐምሌ 23/2017

የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በሶማሌ ክልል እናሳርፋለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የውብ ባህል ባለቤት፣ የአብሮነትና የሰላም ማዕከል፣ የምስራቋ ብርሃን፣ የአያሌ የተፈጥሮ ፀጋ ባለቤት እና የለም መሬት መገኛ በሆነው የሶማሌ ክልል ርዕሰ ከተማ ነፋሻማዋ ጅግጅጋ ከተማ ገብተናል ብለዋል፡፡

የክልሉ ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ሙሃመድ፣ካቢኔያቸው እና የጅግጅጋ ከተማ ህዝብ በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ላደረጉላቸዉ ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቆይታችንም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችና የኮሪደር ልማት የስራ ሂደትን የምንመለከት ሲሆን ታሪካዊውን “በመትከል ማንሰራራት” በ7ኛ ዓመት 700 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር ከሶማሌ ክልል ህዝብ ጋር አብረን የምንከውን ይሆናል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review