ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጅግጅጋ ከተማ ኮሪደር ልማት የምስራቋን ኮከብ ወርቃማ የውበት ድባብ አልብሷታል ሲሉ ገለጹ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጅግጅጋ ከተማ ኮሪደር ልማት የምስራቋን ኮከብ ወርቃማ የውበት ድባብ አልብሷታል ሲሉ ገለጹ
  • Post category:ልማት

AMN ሃምሌ 23/2017

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጅግጅጋ ከተማ ኮሪደር ልማት የምስራቋን ኮከብ ወርቃማ የውበት ድባብ አልብሷታል ሲሉ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በከተማዋ በምሽት ተዘዋውረን ባደረግነው ምልከታ ከስምንት ወራት በፊት በሁለት ምዕራፍ የተጀመሩ ስራዎች በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ መሆናቸውን አይተናል ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን የአስፋልት መንገዶች ያሰፋ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችንም ያካተተ ነው።

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችን ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።

የወጣቶችና ታዳጊዎች ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ጣቢያዎችም በመገንባት ላይ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

ከተማዋ ለክልሉ ከተሞች ሞዴል በሚሆን መልኩ ሰፊ የልማት ጎዳና ላይ ስትሆን የከተማዋ የቆየ ችግር የነበረውን ጎርፍ ለመከላከል የሚያስችሉ ማፋሰሻዎች፤ የተቀናጀ የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮምና የመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታዎችም ይበሉ የሚያሰኙ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ባለሀብቶች በከተማዋ በሆቴል አገልግሎት እና ሌሎች ዘርፎች ተሰማርተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታን እየፈጠሩ ይገኛሉ ብለዋል በመልዕክታቸዉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review