ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛዉ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብርን በጅማ ከተማ አስጀምረዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) : ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታናቸዉና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በሃገር አቀፍ ደረጃ በ7ኛዉ ዓመት የአረንጓዴ አሻራ 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ከማለዳዉ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመላዉ ሃገሪቱ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡