ማህበረሰቡ በጋራ ተስማምቶ ከሰራቸው ትላልቅ ሀገራዊ አጀንዳዎች ውስጥ አንዱ አረንጓዴ አሻራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing ማህበረሰቡ በጋራ ተስማምቶ ከሰራቸው ትላልቅ ሀገራዊ አጀንዳዎች ውስጥ አንዱ አረንጓዴ አሻራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

ማህበረሰቡ በጋራ ተስማምቶ ከሰራቸው ትላልቅ ሀገራዊ አጀንዳዎች ውስጥ አንዱ አረንጓዴ አሻራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብርን በግንፍሌ ቀበና ወንዝ ዳርቻ አስጀምረዋል፡፡

በምርሐግብሩም፣ መላው ኢትዮጵያውያን ባለፉት 6 ዓመታት በመላው የኢትዮጵያ አካባቢ በተከልናቸው ችግኞች ታላቅ ገድል ሰርተናል ይዚህም ዓለም ላይ የሚያስደምም ድንቅ ስራ ነው የተሰራው ሲሉም ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡

ይህንኑ ታላቅ ገድል በ2017 ዓ.ም እየደገምን ነው ያለነው ያሉት ከንቲባዋ፣ ችግኝ በመትከላችን የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብርን ጥብቅ በሆነ መንገድ ይዘን ያለ ፆታ፣ ዕድሜ ፣ ብሔር፣ ሃይማኖት እና ፖለቲካ አመለካከት የተተከለው ትልቅ አሻራ ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር መሆኑን አንስተዋል፡፡

አረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር መሆን እንዲችል የሚያደርግ ፅኑ መሰረት የተጣለበት እንደሆነም ነው ያመላከቱት፡፡

የምንተክለው ጥላ ብቻ አይደለም፣ ውበት ብቻ አይደለም፣ ለጫካ የሚሆን ዛፎች ባቻ አይደለም ያሉት ከንቲባዋ፣ የምንተክለው ምግባችንንም በመሆኑ የምግብ ዋስትናችንንም የምናረጋግጥበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review