የሚተከሉት ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ መሆናቸውን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ

You are currently viewing የሚተከሉት ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ መሆናቸውን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ

‎AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

‎የምንተክላቸው ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ ናቸው ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ዕቅድ በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል::

አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የችግኝ ተከላ ተግባር በአንድ ጀንበር በማካሄድ የሚያበቃ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት የተተከሉትን መንከባከብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የመሬት መራቆት ብዝሃ ህይወትን ስጋት ላይ እንደሚጥል ጠቅሰው፣ አካባቢያችንን ለማስዋብና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽዕኖን ለመቋቋም ችግኝ ተከላን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

በአረንጓዴ አሻራ የበኩላችንን በመወጣት ለነገ ትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋት እናስቀምጥ ሲሉ ‎ርዕሰ መስተዳደሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review