የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተፈጥሮ ሃብትን የመጠበቅና የምግብ ዋስትና መሰረት መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ

You are currently viewing የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተፈጥሮ ሃብትን የመጠበቅና የምግብ ዋስትና መሰረት መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተፈጥሮ ሃብትን የመጠበቅና የምግብ ዋስትና መሰረት መሆኑን የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ።

”በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር በሀገሪቷ ሁሉም አካባቢዎች እየተከናወነ ይገኛል።

በአፋር ክልልም ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፤ በዱብቲ ወረዳ አይሮላፍ ቀበሌ በመገኘት አሻራቸውን አኑረዋል።

ከዚሁ መርሃ ግብር በኋላ ባስተላለፉት መልእክትም የአረንጓዴ አሻራ ልማት የተፈጥሮ ሃብትን የመጠበቅ፣የምግብ ዋስትና መሰረት እና የአየር ንብረት ለውጥን የመከላከል ጥረት መሆኑን ተናግረዋል።

በመሆኑም በመትከል ሁላችንም አሻራችንን በማኖር የኢትዮጵያን ብልጽግና እና ማንሰራራት እውን ማድረግ አለብን ብለዋል።

ባለፉት አመታት የተተከሉ ችግኞች ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ መሆኑን አንስተው፥ የዘንድሮው ተጨማሪ አቅም መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ በአፋር ክልል በስፋትና በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተው፥ በመትከልና በመንከባከብ ለጥቅም እንዲበቁ የሁላችንንም ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።

በዚሁ ስፍራ ላይ በመገኘት አሻራቸውን ያኖሩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ፥ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ ልማት የተከናወኑ ስራዎች ስኬታማ መሆናቸውን አንስተዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተሰሩ ስራዎች የተፈጥሮ ጥበቃ ስራ እየተጠናከረ፣የምግብ ዋስትና መሰረት እየሆነ መጥቷል ብለዋል።

በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ በተካሄደው መርሃ ግብር የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኀላፊዎች፣የመከላከያ እና የፌዴራል ፖሊሰ አባላትና አመራሮች አሻራቸውን አኑረዋል።

#ከማምረትበላይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review