የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖን ለመቋቋም ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው

You are currently viewing የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖን ለመቋቋም ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው

‎AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖን ለመቋቋም ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ገልፀዋል።

በድሬዳዋ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

‎በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ በ4ኛው የናፍቆት ድሬ ለመሳተፍ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የድሬዳዋ ተወላጅ ዳያስፖራዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳትፉ ነው፡፡

‎ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ ለተከታታይ ዓመታት እየተካሄደ የሚገኘው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የሀገሪቱን አየር ንብረት ከማስተካከል ባለፈ ለሌሎች ሀገራትም ተምሳሌት ነው ብለዋል፡፡

‎በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞች እየተተከሉ ይገኛል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review