ዛሬ የምንተከላቸዉ ዛፎች ለነገ ልጆቻችን እና ለሀገራችን መሠረቶች መሆናቸውን ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ

You are currently viewing ዛሬ የምንተከላቸዉ ዛፎች ለነገ ልጆቻችን እና ለሀገራችን መሠረቶች መሆናቸውን ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃግብር እያካሄዱ ነው።

በመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪየም እየተካሄደ ባለው የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የጸጥታ አካላት፣ የሀይማኖት አባቶች እና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል የተወጣጡ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች እንደ ሀገር በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል የተያዘውን እቅድ ከግብ ለማድረስ ከጠዋቱ 12 ጀምሮ ነው መርሃ ግብሩን እያካሄዱ ያሉት።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ ዛሬ የምንተከላቸዉ ዛፎች ለነገ ልጆቻችን እና ሀገራችን መሠረት ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያን አረንጓዴ ለማድረግ በተሰራው ስራ የአረንጓዴ ሽፋንን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉንም ገልጸዋል።

የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ተፈጥሮን የመንከባከብ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ በበኩላቸው፣ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በዚህ ዓመት ከግማሽ ሚሊየን በላይ ችግኝ መተከሉን ገልጸዉ፣ በዛሬው እለትም 53 ሺ ችግኞች እንደሚተከሉ ተናግረዋል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ 28 ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን ያብራሩ ሲሆን፣ ችግኞችን ከመትከል ባሻገር በማልማት የታሰበላቸውን ግብ እንዲመቱ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review