የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብር የኢትዮጵያን ማንሰራራት ከሚያበስሩ መርሃ ግብሮች አንዱ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለፁ

You are currently viewing የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብር የኢትዮጵያን ማንሰራራት ከሚያበስሩ መርሃ ግብሮች አንዱ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለፁ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን ማንሰራራት ከሚያበስሩ መርሃ ግብሮች አንዱ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

በክልሉ እየተካሄደ ባለው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ርዕሰ መስተዳድሩ በአቡራሞ ወረዳ ተገኝተው ዐሻራቸውን ማኖራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለፁት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የክልሉንና አጠቃላይ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን የሚያሳድግና የምግብ ዋስተናን ለማረጋገጥ የሚያግዝ ነው።

መርሃግብሩ የኢትዮጵያን ማንሰራራት ከሚያበስሩ መርሃ ግብሮች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመው፤ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በክልሉ የሚካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብር በተለይም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በደለል እንዳይሞላ የሚያግዝ በመሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ እንዳለው አክለዋል።

በክልሉ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ለምግብነትና ለደን ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች በሁሉም አካባቢዎች እየተተከሉ መሆኑን ጠቁመዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review