የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተፈጥሮ ስነ-ምህዳርን ለመጠበቅ እንደሚያግዝ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ተናገሩ፡፡
በክልሉ በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጀምሯል፡፡
በኮምቦልቻ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን ያስቀመጡት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እንደገለጹት፣ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተፈጥሮ ስነ-ምህዳርን በመጠበቅ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸው፣ ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ ለመጭው ትውልድ አሻራ እናስቀምጥ ብለዋል።