የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለሐረሪ ክልል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እየሰጠ ነው ሲሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር ገለጹ

You are currently viewing የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለሐረሪ ክልል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እየሰጠ ነው ሲሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር ገለጹ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

በክልሉ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በሰፊው እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር፣ የአረንጓዴ ዐሻራ በክልሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም የጠፉ ምንጮችን በመመለስ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን እያጎለበተ ነው ብለዋል።

በዚህም የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት እያሸጋገረ ነው ሲሉ አውስተዋል።

የአፈር መሸርሸርን በመከላከል እንዲሁም በረሃማነትን በመቅረፍ ልምላሜን እያጎለበተ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በዛሬው እለትም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ጌቱ ወዬሳ በበኩላቸው፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲለሙ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል።

በተለይም ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን የእንክብካቤ ስራውም በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አካል በሆነው በክልሉ ሶፊ ወረዳ ቂሌ ቀበሌ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በመተከል ላይ ናቸው ብለዋል።

“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ በክልሉ በተጀመረው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ አመራሮችን ጨምሮ አርሶ አደሮች፣ ወጣቶችና ሴቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የፀጥታ አካላትና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችም ተገኝተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review