የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ አመራሮችና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸዉን አኖሩ

You are currently viewing የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ አመራሮችና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸዉን አኖሩ

AMN ሐምሌ 24 2017 ዓ.ም

700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር ተልዕኮን ለማሳካት “በመትከል ማንሰራራት!” በሚል መርህ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ አመራሮችና ሰራተኞች በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ችግኞችን ተክለዋል።

የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ከአመራሩና ሰራተኞቹ ጋር በመሆን በቦታው በመገኘት አሻራቸውን አኑረዋል።

ችግኞችን በጋራ መትከል ማህበራዊ ግዴታን ከመወጣት ባሻገር ማህበራዊ መስተጋብርን የሚያጠናክር በመሆኑ ችግኝ መትከልና መንከባከብ ባህል መሆን እንዳለበት ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ አሳስበዋል።

በመርሃ ግብሩ የምግብና የዛፍ ችግኞች፦ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ዘይቱን፣ ወይራ፣ ፅድ፣ ዘንባባ እና ሌሎች ተተክለዋል፡፡

በቀጣይም ቦታውን ጥበቃ በማድረግ ችግኞቹን በመንከባከብ እንዲፀድቁ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ተጠቁሟል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review