የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በድርቅ የሚጠቁ አካባቢዎችን ለመታደግ የህልውና ጉዳይ ነው – ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ

You are currently viewing የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በድርቅ የሚጠቁ አካባቢዎችን ለመታደግ የህልውና ጉዳይ ነው – ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የሶማሌ ክልልን ጨምሮ በድርቅ የሚጠቁ አካባቢዎችን ለመታደግ የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ገለጹ።

የ2017 ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አካል የሆነው በአንድ ጀንበር ሰባት መቶ ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በሶማሌ ክልል እየተካሄደ ይገኛል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ማስተባበሪያ ሀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በስፋት እየተካሄደ ይገኛል።

በክልሉ በአንድ ጀንበር ሰባት መቶ ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር ላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ተማሪዎች፣ ህጻናት፣ የጸጥታ ሃላፊዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የሶማሌ ክልልን ጨምሮ ቆላማ ለሆኑ አካባቢዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አንስተዋል።

መርሃ ግሩ በድርቅ የሚጠቁ አካባቢዎችን በመታደግ የሶማሌ ክልልን ጨምሮ የህልውና ጉዳይ እንደሆነ በአጽንኦት አንስተዋል።

በተመሳሳይ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የሚመጡ አደጋዎችን ለመከላከል ቁልፍ መፍትሄ በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የ2017 አመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አካል የሆነው በአንድ ጀንበር ሰባት መቶ ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከጠዋቱ 12 ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ እየተካሄደ ይገኛል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review