ዛሬ ለ7ኛ ዓመት አረንጓዴ አሻራ የማኖር አካል በሆነውና በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞች ተከላ መርሐግብር ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በጉለሌ እንጦጦ ፓርክ ውስጥ ችግኝ ተከላ አካሂደዋ፡፡
ችግኝ መትከል የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ለማጠናከር፣ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባትና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በጣም ወሳኝ ነው፡፡
ዛሬ የሚተከሉ ችግኞች ለቀጣዩ ትውልድ ዘላቂና አስተማማኝ ልማትንና ለሥራና ለኑሮ ምቹ አካባቢን ለትውልድ የማስተላለፍ ታሪካዊ ኃላፊነት አካል እንደሆነም የችግኝ ተከላ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት መላ ሠራተኞችና አመራሮች በዚህ ታሪካዊ የችግኝ ተከላ ሥነ-ሥርዓት የአረንጓዴ አሻራ በማኖራቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡