የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የቱሪዝም ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተናገሩ፡፡
ሰላማዊት ካሳ በሸገር ከተማ አስተዳደር ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ችግኝ ተክለዋል፡፡
ሚኒስትሯ ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እየተከናወነ ያለው ሥራ የቱሪዝም ዘርፉን የስበት አቅም የሚጨምር ነው ብለዋል፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከለውጡ ሂደት ጅማሮ ወዲህ እየተሰሩ ከሚገኙ ለትውልድ ከሚተርፉ በርካታ ኢኒሼቲቮች መካከል ተጠቃሽ መሆኑን አውስተዋል፡፡
መርሐ ግብሩ የተራቆቱ አከባቢዎች መልሰው የሚለሙበት እና መዳረሻዎችም ውበት የሚጎናፀፉበት በመሆኑ ለቱሪዝም ዘርፉ ልማት ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡