ሀገር የምትገነባው በዜጎቿ አብሮነት እና በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ነው ሲሉ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing ሀገር የምትገነባው በዜጎቿ አብሮነት እና በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ነው ሲሉ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ተናገሩ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ ሀገር የምትገነባውበዜጎቿ አብሮነትና እያንዳንዱ ዜጋ በሚያበረክተው አስተዋጽኦ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር እያከናወነ ነው።

ባለፉት ዓመታት በተተከሉ ችግኞች ቁጥር ታሪክ ሰርተናል ያሉት ሚኒስትሯ፣ አረንጓዴ አሻራ የዚህ ትውልድ የወደፊት ምስክር ነው ብለዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም፣ ባለፉት ጊዜያት የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሮች፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጡ ረገድ እገዛ እንዳለው አንስተዋል፡፡

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ በበኩላቸው፣ ያለፈው ትውልድ የሀገርን ዳር ድንበር በመጠበቅ ኃላፊነቱን እንደተወጣ ጠቅሰው፣ የአሁኑ ትውልድ ደግሞ አረንጓዴ የሆነች ኢትዮጵያ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ነው ብለዋል፡፡

ልጅ ዳንኤል እንዳሉት፣ የአሁኑ ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴ ኢትዮጵያን ለማስረከብ የጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች እና በርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብርን በጉለሌ እጽዋት ማዕከል እያካሄዱ ይገኛሉ።

በበላይሁን ፍስሃ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review