የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች እና አመራሮች በአንድ ጀንበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ችግኝ በመትከል ዐሻራቸውን አኑረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ የማህበረሰቡን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ስትራቴጂ ነድፎ ከሚያከናውናቸው ቁልፍ የልማት ዘርፎች መካከል አንዱ አረንጓዴ ዐሻራ መሆኑን ገልጿል፡፡
በ7ኛው ዙር አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ችግኞችን ለመትከል መዘጋጀቱን ገልጾ፣ በዛሬው ዕለት የአንድ ጀንበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተሳትፎ ማድረጉን አስታውቋል።
ኩባንያው ዓለም የደረሰበትን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ከማድረግ ጎን ለጎን በበርካታ ዘርፎች ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የምታደርገውን ግስጋሴ በዘላቂነት ለመደገፍ የሚያስችሉ ቀጣይነት ያላቸው የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ላይ እንደሚገኝ አመላክቷል፡፡