በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 714.7 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል ፡፡
አጠቃላይ 29.7 ሚሊዮን ሕዝብ እንደተሳተፈ የተናገሩት ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ፤ የዛሬው ቀን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሕብረት ታሪክ የሠራበት ዕለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መርሐ ግብሩ እንዲሳካ በማስተባበር እና በመሳተፍ ታሪክ የሰሩ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ አመስግነዋል፡፡