የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላው የኢትዮጵያውያንን አንድነትና አብሮነት የበለጠ የሚያጎለብት ነው

You are currently viewing የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላው የኢትዮጵያውያንን አንድነትና አብሮነት የበለጠ የሚያጎለብት ነው

AMN ሐምሌ 24/2017

የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ የኢትዮጵያውያንን አንድነትና አብሮነት ይበልጥ የሚያጎለብት መሆኑን የሃይማኖት አባቶችና አባገዳዎች ገለጹ።

የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡት መካከል ቄሰ ገበዝ ፍቃዱ ሽመልስ፥ አካባቢን መጠበቅና መንከባከብ ንጹህ አየር ከማምጣት ባለፈ ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ጉልህ ሚና እንዳለው አንስተዋል።

ከዚህ አኳያ የእምነት ተቋማት ችግኝ ለዘመናት ተንከባክበው ማቆየታቸውንም ነው ያስታወሱት።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሼህ ሁሴን በሽር ዛፍ ከሰውና እንሰሳት ህይወት ጋር ከፍተኛ ቁርኝት እንዳለው ጠቅሰዋል።

ችግኝ መትከል ጽዱ አካባቢን የመፍጠር ግብን ለማሳካት እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

አባገዳ ግርማ ገላና በበኩላቸው፥ ችግኝ መትከል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ጠቅሰው፥ የአካባቢ ብክለትን ከመከላከል ባለፈ ለአባገዳዎችና ለአገር ሽማግሌዎች ጥላ መሆኑንም ነው ያነሱት።

የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ የኢትዮጵያውያንን አንድነትና አብሮነት የበለጠ የሚያጎለብት መሆኑንም ነው አስተያየት ሰጪዎቹ ያነሱት።

የተተከሉ ችግኞች የታለመላቸውን ዓላማ እንዲያሳኩ የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

”በመትከል ማንሰራራት” በሚል በአንድ ጀንበር የ700 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ በመላ አገሪቱ እየተከናወነ ይገኛል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review