የአረንጓዴ ዐሻራ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖር የሚችልበትን አካባቢ ለመፍጠር ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ ጫልቱ ሳኒ ገለጹ

You are currently viewing የአረንጓዴ ዐሻራ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖር የሚችልበትን አካባቢ ለመፍጠር ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ ጫልቱ ሳኒ ገለጹ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

የአረንጓዴ ዐሻራ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖር የሚችልበትን አካባቢ ለመፍጠር ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ በሸገር ከተማ በሰበታ ክላስተር በፉሪ ክፍለ ከተማ በአንድ ጀንበር የ700 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መረሐ ግብር ባስጀመሩበት ወቅት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖር እንዲችል ምቹ አካባቢ የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።

አረንጓዴ ዐሻራን ማኖር ብቻ ሳይሆኖን የተፈጥሮ ሚዛንን መጠበቅና መንከባከብ ያስፈልጋል ብለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሰው ልጅ ንጹህ አየርና ውሃ እንዲያገኝ እንዲሁም ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖር እንዲችል የሚያደርግ በመሆኑም አጠናክረን ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል።

አረንጓዴ አሻራ የተፈጥሮ ሚዛንን በመጠበቅ የብልፅግና ጉዞአችንን የምናሳካበት እና ከተሞቻችንን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ፣ ለኑሮ እና ለስራ ተስማሚ እንዲሆኑ ጉልህ ሚና ይጫወታልም ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review