የሚተከሉ ችግኞች ቆጠራ የሚካሄደው በሳይንሳዊ መንገድ መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ካሳሁን ገለጹ

You are currently viewing የሚተከሉ ችግኞች ቆጠራ የሚካሄደው በሳይንሳዊ መንገድ መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ካሳሁን ገለጹ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

‎የሚተከሉ ችግኞች ቆጠራ የሚካሄደው በሳይንሳዊ መንገድ መሆኑን የብሔራዊ አረጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ቴክኒክ ኮሚቴ የቴክኖሎጂ ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ ካሳሁን ገልጸዋል።

‎ክልሎች በራሳቸው ዕቅድ በመያዝ ቦታዎችን ሲለዩ ከዚህ ቀደም ያልተተከለበት ቦታ መሆኑ ተረጋግጦ ካርታ እንደሚሠራለት ባለሙያው ጠቁመዋል።

‎ተከላው ሲጀመር በእያንዳንዱ ሳይት ሪፖርተሮች እንደሚኖሩ የጠቀሱት አቶ ቴዎድሮስ፣ የተከላው ሂደት እና የተተከሉ ችግኞችን መጠን እንደሚገልጹ ተናግረዋል።

‎የመጣው ቁጥር ከተቀመጠው የመሬት ስፋት ጋር ተገናዝቦ በሳይንሳዊ መንገድ እንደሚሰላ እና ቁጥሩ ከተጠበቀው በላይም ሆነ በታች ሲሆን፣ ሲስተሙ እንደማይቀበል ገልጸዋል።

‎በዚህም መሰረት በትክክል የተተከሉት ችግኞች ብዛት ተረጋግጦ ወደ ማዕከል ስለሚመጣ ምንም ዓይነት መዛነፍ እንደማይኖር ባለሙያው አረጋግጠዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review