የአየርላንድ መንግስት የአውሮፓ- አሜሪካ የንግድ ስምምነት በሀገሪቱ ላይ ስለሚኖረው ተፅእኖ ሊመክር ነው

You are currently viewing የአየርላንድ መንግስት የአውሮፓ- አሜሪካ የንግድ ስምምነት በሀገሪቱ ላይ ስለሚኖረው ተፅእኖ ሊመክር ነው

AMN- ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም

በአውሮፓ ህብረት እና በአሜሪካ መካከል የሚደረገው የንግድ ስምምነት፣ በአየርላንድ መንግስት ላይ ስለሚያሳድረው ተጽእኖ እንደሚወያይ አስታውቋል።

በስብሰባው የፋይናንስ ዲፓርትመንት ኃላፊዎች የ15 በመቶ ታሪፍ፣ በአየርላንድ ኢኮኖሚ ላይ ምን ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ትንታኔ እንደሚያቀርቡ ታውቋል።

አየርላንድ ለንግድ ስምምነቱ ምላሽ ለመስጠት የምታካሂደው ውይይት፣ የመንግስት ኤጀንሲዎችን፣ የንግድ ቡድኖችን፣ ማህበራትን እና ከፍተኛ ሚኒስትሮችን ያካተተ ሰባተኛው ውይይት ይሆናል ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ እና የንግድ ሚኒስትር ሲሞን ሃሪስ እንዳሉት፣ የስምምነቱ ማዕቀፍ በዓለም ላይ የተቀናጀ የንግድ ግንኙነትን ለሚወክሉ የአየርላንድ፣ አውሮፓ እና አሜሪካ የንግድ ግንኙነቶች አስፈላጊውን ማረጋገጫ ይሰጣል ብለዋል።

ሃሪስ አክለውም የመነሻ ታሪፉ 15 በመቶ ቢሆንም አሁንም ሙሉ ዝርዝሮችን እየጠበቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በጋራ የተዘጋጀው የድርጊት መርሐ-ግብር የአየርላንድ የንግድ ግንኙነቶችን ከነባር እና አዳዲስ ገበያዎች ጋር ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ታውቋል ሲል አር ቲ ኢ ዘግቧል።

በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ ስለ ስምምነት ማዕቀፉ ዝርዝር ማብራሪያ በጋራ መግለጫቸው ሊሰጡ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በብርሃኑ ወርቅነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review