የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ፖለቲካዊ ነው በተባለለት ሰው ሰራሽ የረሀብ አደጋ ውስጥ ባለችው ጋዛ ያልተለመደ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በጋዛ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስከፊ እየሆነ የመጣው ሰብአዊ ቀውስ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።
ህዝቡ በጣም እንደተራበ እና ሁኔታው አሰቃቂ እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
ሰብዓዊ ቀውሱ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ተከትሎ ሁለት ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ዛሬ ለጉብኝት ወደ ስፍራው ያቀናሉ ተብሏል፡፡
የዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ እና በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ በስፍራው ያለውን የምግብ ስርጭት ተመልክተው ለፕሬዚዳንቱ ሪፖርት እንደሚያደርጉም ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡
በታምራት ቢሻው