የኦሮሚያ ልማት ማህበር አመራሮችና ሰራተኞች በኢትዮጵያ አየር ሀይል የሚሰለጥኑ የኦልማ ተማሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር ሀይል አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ በጉብኝቱ ወቅት በአየር ሀይሉ ግቢ ውስጥ ለሚሰለጥኑ ተማሪዎች የሚሰጠው ስልጠና ተማሪዎች በብዙ መልኩ የተካኑና የሀገር ፍቅር ስሜት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ብለዋል።
የኦልማ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው ስልጠናው ተማሪዎች ከአየር ሀይሉ ማህበረሰብ ልምድ የሚወስዱበት ስለመሆኑም ተናግረዋል። ወደ አየር ሀይሉ ለስልጠና የገቡት ሰልጣኞች ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው የወጡ የኦልማ ተማሪዎች ናቸው ያሉት ደግሞ የኦልማ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ኢቲቻ ናቸው።
በአየር ሀይሉ የሚወስዱት ስልጠና በአካልም ሆነ በአእምሮ የዳበሩ እንዲሆኑ ያስቻላቸዉ ስለመሆኑ የሚገልፁት በኢትዮጵያ አየር ሀይል ስልጠና ሲወስዱ ያገኘናቸው የኦልማ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ናቸዉ፡፡
በአየር ሀይሉ ያገኙት ስልጠና በትምህርት ቤት ውስጥ ካገኙት እውቀትና ክህሎት በላይ የህይወት ተሞክሮና የሀገር ፍቅርን የተማሩበት መሆኑን ለኤ ኤም ኤን ገልፀዋል።