ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ

AMN ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።

በአፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከሐምሌ 23-26 ቀን 2017 ዓ.ም. በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በተካሄደው የኢንተርፓርላማ ሕብረት (IPU) ስድስተኛው የፓርላማ የአፈ-ጉባኤዎች ጉባኤ ላይ መሳተፉ ይታወቃል፡፡

አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጄኔቫ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቋሚ መልዕክተኛ መኖሪያ ቤት በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ላይ አምባሳደሮች፣ ከሚሲዮኑ ሰራተኞች እና በስዊዘርላንድ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር ተሳትፈዋል።

ፕሮግራሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል የተቀመጠውን መርሀግብር ለመቀላቀል ያለመ ነው፡፡

አቶ ታገሰ ጫፎ በጄኔቫ ስዊዘርላንድ የኢንተርፓርላማ ሕብረት (IPU) ስድስተኛው የአፈ-ጉባኤዎች ኮንፈረንስ ላይ ተሳትፎ ለማድረግ በሄዱበት ወቅት አረንጓዴ አሻራቸውን ከሚሲዮኑ ጋር ለማኖር መልካም አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አፈ ጉባኤው አፅንኦት መስጠታቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review