እንደ ሀገር ለተመዘገቡ የልማትና ዲሞክራሲ ግንባታ ስኬቶች፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና ከፍተኛ መሆኑን ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing እንደ ሀገር ለተመዘገቡ የልማትና ዲሞክራሲ ግንባታ ስኬቶች፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና ከፍተኛ መሆኑን ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናገሩ

AMN- ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እንደ ሀገር የተመዘገቡ በርካታ የልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ስኬቶች፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዕቅድን በአዳማ ከተማ እየገመገሙ ነው።

የተቋሙ የዘንድሮ አፈጻጸም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ውጤታማ የኮሙኒኬሽን ሥራዎች የተመዘገቡበት ዓመት መሆኑ በግምገማው ታይቷል፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር)፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እንደ ሀገር የተገኙ የልማትና ዲሚክራሲ ግንባታ ሥራዎች አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግበዋል ብለዋል፡፡

በተለይ ዜጋ ተኮር የሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ፣ በውጭ ንግድ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መረሐ ግብርና ሌሎች የልማት ኢኒሼቲቮች ተግባራዊ መደረጋቸው፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ተጨባጭ ለውጦች መታየታቸው፣ እንዲሁም በሰው ሀበት ልማትና በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ድርብርብ መሆናቸውን ዶክተር ለገሠ ገልጸዋል።

ከተገኙ ውጤቶች ጀርባ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና ከፍተኛ እንደ ነበርም ሚኒስትሩ አስታውሰዋል፡፡

በቀጣይ ጊዜያትም በሁሉም ዘርፎች የሀገሪቱ የማንሰራራት ዘመን ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ አሠራርና አደረጃጀት ይበልጥ የማጠናከር ሥራ በትኩረት የሚሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ ይበልጥ ለማሳለጥ አጠቃላይ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቀናጅተው እንዲሠሩ ከማድረግ አንጻር በትኩረት እንደሚሠራም አስገንዝበዋል፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳም፣ ባለፈዉ ዓመት ዘርፉን አቀናጅተው ለመምራትና ዐቅም ከመገንባትና የመንግሥት መረጃዎችን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል፡፡

እንደ ሀገር ዘርፉ ከተጣለበት ኃላፊነት አኳያ በቀጣይ በላቀ ደረጃ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው መሥራት ይጠይቃል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ዐጠቃላይ የዘርፉን አሠራሮች ለማዘመን የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት የሚሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተቋሙ ሥራ አመራር ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸዉ ፀጋዬም የበጀት ዓመቱን የዕቅድ ክንዉን አቅርበዉ በሠራተኞች ውይይት መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review