ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉት የአራት ኪሎ የገበያ ማዕከላት፣ የመኪና ማቆሚያዎች እና ፕላዛዎች ለህዝባችን የላቀ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው መሆናቸዉን ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል፡፡
ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ እነዚህ መሰረተ ልማቶች የአከባቢውን ታሪካዊ ይዘትን ያማከሉ ፣ አራት ኪሎን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚያስተሳስሩ ናቸዉ ማለታቸዉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡